ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
96

በምዕ/ጐ/ዞን የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒዬን ኃ.የተ. የ2017 ዓ.ም በጀት አገልግሎት የሚሰጡ ሎት 1 የጽህፈት እና የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 2 የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ ሎት 2፡1 የተለያዩ የመኪና ጎማዎች፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 4. ህትመት፣ ሎት 5 የተዘጋጁ አልባስት፣ ሎት 6 ፈርኒቸሮች እና ሎት 7 የዱቄት ፋብሪካ መለዋወጫዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. በዘርፍ የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ያያይዙ፡፡
  3. የግዥው መጠኑ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ ይጠበቅቦዎታል፡፡
  4. ከላይ ከ1-3 የተዘረዘሩትን የምታሟሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሎት 11 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ስዓት ቅዳሜን ጨምሮ የማይመለስ 00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከዩኒየኑ ዋና መሥሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ሂሳብ ክፍል እስከ 8፡00 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ማንኛውም ተጫራች በሙሉ ዝርዝር ላይ በእያንዳንድ ዋጋ መሙሉት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11 ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን /ካላንደር/ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተጠቀሰው ስዓት ይከፈታል፡፡
  7. የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
  8. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጐልም፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. አሸናፊው የሚለየው በሎት ጥቅል ድምር ነው፡፡
  11. አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር አስር በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  12. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
  14. የማስረከብያ ቦታ ዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ ቡሬ ከሚገኘው ጽ/ቤት ድረስ ይሆናል፡፡
  15. ተጫራቾች ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40 /10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡

የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒዬን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here