ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
84

በምሥራቅ ጎጃም ዞን በደ/ጥ/ግ/ወ/ በቁይ ከተማ መሪ ማዘጋጀ ቤት በ2017 የበጀት አመት በከተማው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ለማሰራት የማሽን ኪራይ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለመንገድ ግንባታ የሚያስፈልገው ማቴሪያል ወይም ጠጠር የሚመረትበትን ቦታ ማዘጋጃ ቤቱ የሚያሳይ ሲሆን በጥራት የሚሰራ ሆኖ ከተጫራቾች መካከል አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ የማሽን ፈቃድ ያላቸው አካላት ማጫረት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተራጫራቾች ማወዳደር ይፈልጋል፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የማሽን ኪራይ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የሞሉት ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. በወጣው የሥራ ዝርዝር መሰርት ሁሉንም ወጭ የሚችል ማለትም ለመንገድ ሚያስፈልገውን ነዳጅ እና የማሽኖች ማምጫና መውሰጃ (ሎቬድ) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በቁይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይቻላል፡፡
  5. ተጫራቾች ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ሁኖ የጠቅላላ ግዥዉን ግምታዊ ዋጋ መሰረት በማድረግ ከዜሮ ነጥብ አምስት በመቶ ያላነሰ እና ከሁለት በመቶ ያልበለጠ የገንዘብ መጠን ተወስኖ በጨረታ ጥሪዉ እና ሰነድ ዉስጥ መገለጽ አለበት፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወጥ የሆኑ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቁይ መሪ ማዘጋጃ ቤት በተዘጋጀው የግዥ ጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ስማቸዉን፣ ፊርማቸዉን ፣ሙሉ አድራሻቸዉን እና የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት ፓስታ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  9. ይህ ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 21 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. የማሽን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  11. ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ፀንቶ የሚቆይበት በ21 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
  12. ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ ቢሮ ቁጥር 07 ጋዜጣው በወጣ በ22ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ላይ የሚከፈት ሲሆን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች ባወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
  14. በዉድድሩ የተገኘዉ ዋጋ ሳይቀየር መ/ቤቱ ሃያ በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡
  16. አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ዝቅተኛ ዋጋ /ሎት/ ሞልቶ ካቀረበ ይሆናል፡፡
  17. አሸናፊው ተጫራች ወይም ድርጅት ለመንገድ የሚያስፈልጉ ማቴሪያል ወይም ቁሳቁስ ትራንስፖርት ቦታው ድረስ እራሱ የሚያጎጉዝ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  18. አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ከ5 የሥራ ቀናት በኃላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መያዝ አለበት፡፡
  19. ተጫራቾች የጨረታውን መጠን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  20. ሥርዝ ድልዝ ካለው ልዩ ፍሪማ መቀመጥ አለበት ልዩ ፊርማ ከሌለው ተቀባይነት የለውም፡፡
  21. አድራሻችን በአማራ ክልል በምሥራቅ ጎጃም ዞን/ደ/ጥ/ግ/ወ/ቁይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ከአዲስ አበባ 284 ኪ/ሜትር ከባህር ዳር 324 ኪ/ሜትር ከደብረማርቆስ – ቁይ 60 ኪ/ሜትር ላይ ትገኛለች፡፡
  22. ለተጨማሪ መረጃ 09 31 84 25 43 /09 20 50 69 44 መደወል ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ነዳጅ እና የማሽኖች ማምጫና መውሰጃ (ሎቬድ)ተጫራቹ የሚችል መሆኑን እንገልጻለን

የቁይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here