ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
98

በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሬድ ፕላስ በጀት ለአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚዉል ሎት 1.Hilux-Revo የመኪና እቃና የመኪና ጎማ ከነካለማደሪያዉ፣ሎት 2. የእንስሳት መድሃኒት በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡

  1. ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. እቃ ወይም የአገልግሎት ግዡ መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርባቸው የጨረታ ሰነዶች ግልጽና የሚነበቡ መሆን አለባቸው፡፡
  4. ጨረታ ሰደነዱን ሲገዙ ለየአንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00.00 (ሁለት መቶ ብር) ለመክፈል ከተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 1. የመኪና እቃና የመኪና ጎማ ከነካለማደሪያዉ ብር 3,000.00 ፣ሎት 2. የእንስሳት መድሃኒት ብር 5000.00 በባንክ በተረጋገጠ ትእዛዝ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቢድ ቦንድ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱን ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች ሰነዱ ላይ የአንድ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ከሆነ ከጭረታው ውጭ ይሆናል፡፡
  9. አሸናፊው የሚለየው በሎት (በድምር ዋጋ ነው)፡፡ በሰነዱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ በሙሉ ያልሞላ ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡ አሸናፊ ተጫራች መ/ቤቱ በጠየቀው እስፔስፊኬሽን መሰረት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  10. ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ሲነፃጸር የተጋነነ ከሆነ ጨረታው ውድቅ ይሆናል፡፡
  11. ሁሉም የሚቀርቡ እቃዎች ጥራታቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው፡፡
  12. አሸናፊው ድርጅት እቃዎችን ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሱ አጓጉዞ በማቅረብ ንብረቱን በየንብረት ክፍል አስረክቦ ገንዘቡን ወጭ አድርጎ ይወስዳል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. የእንስሳት መድሃኒት በሚመለከት የአገልግሎት ጊዜው አጭር መሆን የለበትም፡፡
  15. ጨረታውን ለማዛባት የሞከረ  ከጨረታው ውጭ ሆኖ ወደፊትም በመንግስት ጨረታ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
  16. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል የማይችል ሲሆን በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን ዋጋና መግለጫ ማሻሻል አይችልም፡፡
  17. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0332220012 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ /ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here