ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
94

በአብክመ የፖሊስ ኮሚሽን በ2017 በጀት ዓመት ለኮሚሽኑ ሰራተኞች አገልግሎት የሚውል ሎት 1. የደንብ ልብስ ፣ ሎት 2. የጽዳት እቃዎች እና ሎት 3. የጽህፈት እቃዎች በነጠላ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዝቅተኛ ዋጋ ካቀረበዉ ድረጅት መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል ፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው ፡፡
  4. የግዥው መጠን ብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ  የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የሚነበቡ /በደንብ የሚታይ/ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. በጥቃቅን እና አነስተኛ የሚወዳደሩ የንግድ ፈቃዳቸው 5/ አምስት ዓመት/ ያልሞላው ለመሆኑ ከቴክኒክና ሙያ ጽ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ አለባችው፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ላይ የሚገለጸውን ዋጋ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 128 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን በሎጀ/ ፋይ/አስ/ ም/ዘርፍ ወይም ቢሮ ቁጥር 103 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
  10. ተጫራቾች በሎት 1 የተገለጸው የደንብ ልብስ በ4 ወር ወይም ለተከታታይ 120 ቀናት ውስጥ እንዲሁም በሎት 2 እና በሎት 3 የተገለጹትን ለ1ወር / ለተከታታይ 30 ቀናት / ውስጥ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት ፡፡
  11. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16 ኛው ቀን ጧት 3.30 ተዘግቶ በእለቱ ከሰዓት 8.30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡እለቱ በአል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል ፡፡ ነገር ግን በሎት 1. የተገለጸው የደንብ ልብስ በጨረታ ሰነዱ ላይ በሚገለጸው ቀን የሚከፈት ይሆናል ፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 103 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 0582262111 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0582201453 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here