በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የተስፋዬ ጌታቸው መታሰቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ እና በውስጥ በጀት ለተስፋዬ ጌታቸው መታሰቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 እስቴሽነሪ ፣ሎት 2 የጽዳት እቃዎች ፣ሎት 3 ህትመት እና ሎት 4 የመብራት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡- ተጫራቾች ማሟላት የሚፈለግባቸው መስፈርቶች
- ህጋዊና ወቅታዊ የታደሰ የዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈለና ቲን ካርድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችሉ እና አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውንና ሌሎች መረጃዎችን በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡20 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
- የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኃላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ /ማሻሻያ/ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም በመንግስት የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፍ የሚደርጉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ ቢገኙም ባይገኙም ይከፍታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 26 መውሰድ ይቻላል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 058 667 06 35 ዘወትር በሥራ ሰዓት መደወል ይችላሉ፡፡
የተስፋዬ ጌታቸው መታሰቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል