የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ ሴ/መስሪያ ቤቶች በ2014 የበጀት ዓመት ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ እና ሎት 2 የስፖርት ትጥቅ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን/ ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ክጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 14/04/2017 ዓ.ም እስከ 2/05/2017 ዓ.ም የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የማይመለስ00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 26 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የጠ/ድምር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከዋና ገ/ያዥ በደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በ2 ኮፒ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ኦርጅናል ሰነዱ ውስጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 35 የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት እስከ 02/05/2017 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 03/05/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ቢኖሩም ባይኖሩም ይክፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 35 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 817 00 86 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የጨረታ ውጤቱን በጠቅላላ ድምር ውጤት ያያል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ንብረቱን ደ/ከ/አስ/ገን/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 34 ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በመጫረቻ ሰነዶቻቸው ላይ ሙሉ ስማቸውን ፊርማቸውን እና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
የደባርቅ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት