ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
118

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን /ገ/ኢ/ት/መምሪያ የጠገዴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት አመት በሥሩ ለሚገኙ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽሕፈት መሣሪያ፣ ሎት 2 የግንባታ እቃ፣ ሎት 3 የጽዳት እቃ፣ ሎት 4 ብትን ጨርቅ፣ ሎት 5 የተዘጋጁ አልባሳት፣ ሎት 6 የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር፣ ሎት 7 የውጭ ፈርኒቸር፣ ሎት 8 የኤክልትሮኒክስ እቃዎች እና ሎት 9 የመኪና እቃ መለዋወጫ አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተለውን መስፈርቶች የምታሟሉ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የንግድ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ጨረታውን ለማሸነፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 ተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. እቃዎቹ በሙሉ ኦርጅናል እና አንደኛ መሆን አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል በጠ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት ደጋፊ የሥራ ሂደት በመቅረብ ከ21/04/2017 ዓ.ም እስከ 5/05/2017 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማሸግ በጠ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 5/05/2017 ዓ.ም ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጠ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በቀን 06/05/2017 ዓ.ም በ8፡00 ታሽጎ በ8፡30 ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ  አማራጭ  ከአገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. አሸናፊ ድርጅቱ የሚሆነው ከወረዳው ድረስ በመቅረብ ውል መውሰድ እና ንብረቱን ማቅረብ የሚችል፡፡
  13. ጨረታው የሚለየው በሎት በመሆኑ ዋጋውን ሲሞሉ ከፋፍለው መሙላት አይቻልም፡፡
  14. በሎት 4 እና 5 የተጠቀሰው የደንብ ልብስ ጽ/ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት ይሆናል፡፡
  15. በሎት 9 የተጠቀሰው የመኪና አቅርቦት እቃው የሚቀርበው የጥገና ጋራዥ በሚገኝበት ጎንደር ከተማ ይሆናል፡፡
  16. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በጠ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 272 00 14 /09 53 24 40 07 በመደወለወ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጠገዴ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here