ለመጀመሪያ እና ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
113

በአብክመ በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኙው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ ሎት 1 የኤፌሳር መኪና መለዋወጫ እቃ ግዥ፣ ሎት 2 የኤፌሳር መኪና ጥገና (ሰርቪስ) እና ሎት 3 የአፈረ ማዳበሪያ ማከማቻ መጋዝን ኪራይ /የአገልግሎት/ ግዥ በግልጽ በጋዜጣ  አወዳድሮ በአሽናፊው የሚገዛን መግዛት ፣የሚጠገነውን ማስጠገን እና የምንከራየውን መከራየት ይፈለጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  2. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራቲ /ዋስትና/ ወይም /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅርቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. በጋዜጣ የወጣው ግልጽ ጨረታ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለበት፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዝ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል /ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
  6. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለሁለተኛ ጊዜ ለወጣው ለ7 ተከታታይ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 106 ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ  የሚከፈት ሲሆን ለሁለተኛ ጊዜ የወጣው 7 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 7ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ7ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ  ይከፈታል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሎት 1 እና 2 ሲሆን ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ሎት 3 ነው፡፡
  8. ቅዳሜ የዩኒየኑ የሥራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. የጨረታው ተወዳዳሪዎች /ተወካዮቻቸው/ በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  10. የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ አስር በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
  11. አሽናፊ የሚለየው በተናጥል ይሆናል፡፡አሽናፊው የአሸነፈውን በፍትህ ውል ከተመረመረ (ከተመዘገብ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል /ይሸፍናል፡፡
  12. የሚፈልጉትን ሎት መርጦ መሙላት የሚቻል ሲሆን የንግድ ፈቃዱ የማይጋብዝ ካልሆነ በስተቀር ከአንድ ሎት ውስጥ ግን ለይቶ ወይም ቀንሶ (መርጦ) መሙላት አይቻልም፡፡
  13. የአፈረ ማዳበሪያ ማከማቻ መጋዝን ኪራይ የመያዝ አቅሙ 30,000.00 ኩ/ል እና በላይ የሆነ ሲሆን የማከራየት ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡ ስፔስፊኬሽን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡
  14. አሽናፊው የአሽነፈውን እቃ በእራሱ ትራንስፖረት አጓጉዞ ሊያቀርብ እና የሚጠገነውን ለመጠገን ነው፡፡ ማንኛውም ወጭ አሸናፊ የሸፍናል፡፡ የሚገዙት የማንኛውም እቃዎች መጠንና ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡
  15. በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማህበራት የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
  16. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  17. ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 09 11 59 05 34 /09 18 27 83 96 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here