ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
94

በአብክመ የባህር ዳር ከተማ መሰረተ ልማት መምሪያ ፤ የባህር ዳር ከተማ አካ/ጥ/ጽ/ ው/ ጽ/ቤት፣ የአገልግሎት አቅርቦት ፅ/ቤት ፤ ህንፃ ሹም ጽ/ቤት እና ቤቶች ልማት ተጠሪ ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት ለአገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያ፣ የፕሪንተር ቀለም እና የጽዳት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. ግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የገዥው መጠን ብር 200,00/ሁለት መቶ ሺህ/ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የገዥው መጠን ከ20,000.00 /ሃያ ሺህ / ብር በላይ ከሆነ የቫት/7.5 በመቶ/ይቆረጣል፡፡
  5. የሚገዛው እቃ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) በጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፤ ሁሉንም እቃዎች በኦርጅናል መሞላት አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመስስ ብር 00 /አምስት መቶ / ብር ለሶስቱ ሎት  ከፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 206 በመክፈል ሰነዱን 206 ቁጥር ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበት ለሎት የጽህፈት መሳሪያ 40,000.00/አርባ ሺህ ብር/፣ ለሎት 2. የፕሪንተር ቀለም 20,000.00/ሃያ ሺህ /ብር፣ለሎት 3. የጽዳት እቃዎች 20,000.00/ ሃያ ሺህ /ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ኦርጅናል ሰነዱን በግልጽ ፅሁፍ ኢንቨሎፑ ላይ በመፃፍ ማስታወቂው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በባህር ዳር ከተማ መሰረተ ልማት መምሪያ በግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 205 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ን/አስ ቡድን በቢሮ ቁጥር 205 በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊው የሚለየው ለተጠየቁት ጠቅላላ ዕቃዎች በሙሉ ዋጋ በሎት ድምር በዝቅተኛ ዋጋ  ነው፡፡ በዚህ መስፈርት መሠረት በሎት ለተጠየቁት ሁሉም እቃዎች ዋጋ ያላቀረበ እና በተቀመጠው ዝርዝር መገለጫ መሰረት ዋጋ ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  11. ስርዝ ድልዝ የበዛበት እና አጠራጣሪ ቁጥር ያለው የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 205 ድረስ በአካል በመገኘት፣ በመላክ ወይም በስ/ቁ/ 058-220-16-93 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
    የባህር ዳር ከተማ መሰረተ ልማት መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here