ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
87

የላይ ጋይንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን በ2017 ዓ.ም በጀት አመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ምድብ 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ምድብ 2 የጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መወዳደር የሚፈልጉ ማንኛውም ድርጅት መጫረት የሚችል መሆኑን እየገለፅን፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ /ቲን/ ያላቸው፡፡
  3. የሚያቀርቡት እቃ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳታፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙት እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱን የማይመለሥ00 /አንድ መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል ላይ ጋይንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ እና ንብረት አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ እና በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ለእቃዎቹ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ኦርጅናልና ቅጅ በማለት በተለያዩ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ላ/ጋ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው በ16ኛው ቀን በ3፡30 ይዘጋና በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን በ4፡00 ላ/ጋ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ከመከፈቱ አይስተጓጐልም፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. አሸናፊው ድርጅት የአሸነፈውን እቃዎች በየፑሉ ማድረስ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  13. ከጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  14. ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  15. ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ዋጋ ነው፡፡
  16. በማስታወቂያ ያልተገለፁ ሌሎች ካሉ በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  17. ከሎቱ ውስጥ ያንዱን እቃ ዋጋ ካልሞሉ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
  18. ሥለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ላ/ጋ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ቢሮ ቁጥር 4 ድረሰ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 445 13 99 /058 445 00 05 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

ላይ ጋይንት ወረዳ ገንዘብ /ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here