የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
137

በደቡብ ወሎ ዞን የወገልጤና ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታ በሊዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር  721/2004 አንቀጸ 8 ንዑስ አንቀፅ  1 እና  2 ደንብ ቁጥር  103/2004 መመሪያ ቁጥር 1/2005 መሰረት  በ2017 በጀት ዓመት 1ኛ  ዙር ጨረታ

  1. ለሁለገብ ሆቴል አገልግሎት ለB+G+7 እና በላይ ግንባታ የሚውል 1 (አንድ) ቦታ ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ 2. ለሆቴል አገልግሎት ለG+4 እና በላይ ግንባታ የሚውል 1 (አንድ) ቦታ 3. ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል G+0 እና በላይ ግንባታ የሚውል 2 (ሁለት ቦታ) በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
  2. መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች በጋዜጣ ከወጣበት 21/04/2017 ዓ.ም ቀን ጀምሮ ባሉት  10 የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 800.00 (ስምንት መቶ ብር) በመክፈል ወገልጤና ከተማ አሰተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 መግዛት ይቻላል፡፡
  3. የጨረታ ሰነድ ማሰገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ብቻ ወገልጤና ከተማ አሰተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው ሳጥን ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው (ማለትም 30/04/2017 የሥራ ቀን 11፡00 ላይ ይሆናል፡፡
  5. ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው 01/05/2017 የሥራ ቀን በ4፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወገልጤና ከተማ አስተዳደር አዳራሽ ውስጥ ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች ሰነድ በሚገዙበት ጊዜ ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ እና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው መጠን ፣የጠቅላላ የቦታው ስፋት በመነሻ ዋጋው ተባዝቶ ከሚገኝው ውጤት ከሰላሳ በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖረባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የሚቀርቡትን የጨረታ ሰነዶች በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው መሰረት ማሰቀመጥ አለባችው፡፡ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው መሰረት ያልቀረበ ጨረታ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ይሆናል፡፡ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነድ ላይ ማገኘት ይቻላል፡፡
  9. ተጫራቾች የገዟቸውን የጨረታ ሰነዶች ሁሉንም ኦርጅናል መረጃ በሠም በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከፖስታ ውጭ የሚቀርብ መረጃ ተቀባይነት የለውም፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊውን ለመለየት የሚከተሉት የማወዳደሪያ መስፈርቶች መሰረት በማድረግ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ለቦታው ያቀረቡት ዋጋ ሰማኒያ በመቶ የሊዝ ቅድመ ክፍያ መጠን ሃያ በመቶ የሚያዝ ይሆናል፡፡
  11. የግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቂያ ጊዜ በመመሪያ ቁጥር 1/2005 አንቀፅ 47/49 የተቀመጠ ቢሆንም ግንባታውን ገንብቶ በአጭር ጊዜ የሚያስረክብ መሆን አለበት፡፡
  12. ቦታውን ማየት ለሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገልፅ መረሀ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
  13. መ/ቤቱ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ያወጡትን ወጭ የመጠየቅ መብት አይኖራቸውም፡፡
  14. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 335 05 20 /09 20 44 19 35 /09 20 48 42 62 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የወገልጤና ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here