ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
87

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ በሀገር ውስጥ ገበያ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አንደኛ ደረጃ ንፁህ በቆሎ ብጣሪዎችን እና ያገለገሉ ጆንያዎችን ለመሸጥ እንዲሁም የኤሌክትሪክ ዕቃዎች /የህንፃ መሳሪያዎች፣ ኬሚካልና ተዛማች ዕቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡-

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ፣ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት /ቲን/ ፎቶ ኮፒ በማድረግ የማይመለስ00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ባሕር ዳር አለ በጅምላ (ጅንአድ) ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢንተርኘራይዙ መሥሪያ ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች የአሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከኢንተርፕራይዙ ጋር ዝርዝር ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው መሰረት የጨረታውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ በማለት የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመፃፍ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በሥራ ሰዓት በኢንተርኘራይዙ ዋና መሥሪያ ቤት /ባሕር ዳር/ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በአስረኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ይዘጋል፣ በዚሁ ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይሸጋገራል፡፡
  6. ድርጅቶች ዋጋ ከሞሉበት ሰንጠረዥ ላይ እርጥብ ማህተም ወይም ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
  7. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን ዕቃዎች ባሕር ዳር በሚገኘው የኢንተርኘራይዙ ዋና መ/ቤት መጋዝን ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ኢንተርኘራይዙ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ኢንተርኘራይዙ ለግዥም ሆነ ለሽያጭ ከተጠየቀዉ ዉስጥ እንደአስፈላጊነቱ መጠን አስከ ሃምሳ በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  10. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 60 02 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 84 15/ በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here