ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
97

ቁጥር 04/2017

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሎት 1 የጂም ዕቃዎች እና ሎት 2 የሞባይል ጆርናሊዝም ዕቃዎች በድጋሜ የወጣ በግልጽ ጨረታ ዘዴ በጋዜጣ ተጫራቾችን አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት ግዥ መፈጸም ይፈለጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታዉ ለመወዳደር የሚፈለጉ ድርጅቶች፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፊኬት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 104 ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይቻላል፡፡ ለሎት 2 የቴክኒክ ምዘና ለሚያስፈልጋቸዉ ዕቃዎች ብቻ ሰነዱን በመሙላት የቴክኒክ እና የፋይናስ ሰነዶችን ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶችን በጥንቃቄ በፖስታ ለየብቻ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፣ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  4. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥ ክፍል 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /ስፒኦ/ ፣በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈትበት 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡
  7. ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የሚፈለጉት ዕቃዎች ዓይነት ፣ብዛትና ስፔስፊኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በመምጣት መዉሰድ ይቻላል፡፡ በተጨማሪም አዲስ አበባ አሚኮ ቅርንጫፍ 4 ኪሎ አልማ ህንጻ ግራዉንድ ጨረታ ሰነዱን በመግዛት መዉሰድ ይቻላል፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 በፋክስ 058 320 7069 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን    

  ባህር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here