ህንዳዊቷ እማወራ አባወራው ከድመታቸው ጋር ረዘም ያለ ጊዜ በማሳለፍ ትኩረት እንደሚነፍጓቸው በመግለፅ ጨካኝነቱን የሚያመላክት አንቀፅ ጠቅሰው ከፍተኛ ፍርድ ቤት መክሰሳቸውን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ሰሞኑን ለንባብ አብቅቶታል፡፡
ክሱ የቀረበለት የካርናታካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባልተለመደው የቤት ውስጥ የጥንዶች አለመግባባት ጣልቃ ገብቶ አከራክሯል፡፡
ፍርድ ቤቱ ባደረገው ተጨማሪ የማጣራት ሂደት በጥንዶቹ መካከል የተከሰተው የ“ጊዜ አሳንሶኛል” ክስ ከመከረር አልፎ ተርፎ በድመቷ በተደጋጋሚ መቦጫጨቅ እንደደረሰባቸው ተናግረዋል እማወራም፡፡
የከፍተኛው ፍርድ ቤት የመሀል ዳኛ ኤምናጋኘራስ በቀረበው ክስ ምንም አይነት የጭካኔ ድርጊትን መፈፀሙን እንደማያመላክት በመግለጽ አጣጥለውታል፡፡
በአብዛኛው በአገሪቱ እንደሚቀርቡ፣ በመጨረሻም የፍትህ ስርዓቱን ከሚያጨናንቁት ክሶች ጋር የሚመሳሰል ረብ የለሽ መሆኑን በመግለፅ አጣጥለው የክስ መዝገቡ መዝጋታቸው በድረ ገጹ ሰፍሯል፡፡፡፡
(ታምራት ሲሳይ)
በኲር የታኅሳስ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም