የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል ሎት 1 ላፕቶፕ ኮምፒውተር ፣ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያ ፣ሎት 3 የመኪና መለዋወጫ ዕቃ እና እና ሎት 4 የተሸከርካሪ ጎማ ግዥ አገልግሎት የሚሆን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ሰለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ይጋብዛል፡፡
- ቲን የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉና ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ግዥ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ መሆኑ ሲገመት /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 5,000.00 (አምስት ሽህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ መሸጫ ዋጋ00 (አራት መቶ ብር) ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ከ28/04/2017 ዓ.ም እስከ 12/05/2017 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀን ሲሆን በ16ኛው ቀን ይከፈታል፡፡
- ጨረታዉ የሚከፈተዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ13/05/2017 ዓ.ም በ5፡00 ታሽጉ 5፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች /ተወዳደሪ/ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት በ5 ቀን ዉስጥ ከመ/ቤቱ ጋር ዉል መያዝ አለበት፡፡
- የንግድ ፈቃዳቸው ከሚያቀርቡት ዕቃ ጋር ተዛማጅ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ከጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል ቢሮ ቁጥር 10 በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 211 01 45 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል