ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የመደበኛ ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
98

የሞጣ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነገገው እዋጅ ቁጥር 721/2007 አንቀጽ 8 ንዕስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከ ‘’ሀ’’ እስከ ‘’ሠ’’ በተዘረዘረው መሰረት ለመኖሪያና ንግድ አገልግሎቶች የተዘጋጅ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሞጣ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት በሥራ ስዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

  1. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
  2. የጨረታ ሳጥን የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
  3. ቦታውን መጐብኘት ለሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ኘሮግራም በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
  4. ስለ ጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
  5. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 በከተማ አስተዳደሩ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይሆናል፡፡ 11 ኛዉ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  6. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚመለሰው የጨረታ አሸናፊው ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ስዓት ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናና የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት ከአስር በመቶ ያላነሰ በዝግ አካውንት በማስገባት በባንክ የተመሰከረለት (ሲፒኦ) ሰነድ ከዋጋ እና ከሃሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  8. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 661 19 05 /10 89 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የሞጣ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት /ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here