ቁጥር አካ/ደ/ጥ/ል/ባ ግ/03/2ዐ17
በአብክመ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ባለስልጣን እና የጣና ሀይቅና ሌሎች ውሀማ አካላት ጥበቃ እና ልማት ኤጀንሲ በመደበኛ በጀት ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ እስቴሽነሪ ፣ፈርኒቸር እና የጽዳት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ የሆኑ አቅራቢዎችን በዚህ ግልጽ ጨረታ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታውን ሠነድ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ባሕር ዳር ጋንቢ ቲችንግ ሆስፒታል ጎን ካለው በመ/ቤቱ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ፤ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 10 ፤60∙00 /ስልሳ ብር / የማይመለስ በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች የጨረታው ሠነድ በሚጠይቀው መሠረት ሞልተው በታሸገ ፖስታ በማድረግ በ16ኛው ቀን አስከ 3፡00 ድረስ በመ/ቤቱ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 14 አጠገብ ለዚህ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እንዲገባ መደረግ አለበት፤ ጨረታው በእለቱ 3፡30 ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ ተጫራቾች ባይገኙም ከመክፈት አያግድም፡፡
- ተጫራቾች ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ በባንክ ወይም በኢትዩዽያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች ማቅረብ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከመ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ አብረው ማቅረብ አለባቸው የኢንሹራንስ ቦንድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ከ 20 ሺህ ብር በላይ ለሆኑ ግዥዎች የቫቱን 50በመቶ ቢሮው የሚያስቀር መሆኑን ይገልጻል፡፡
- ከብር 200 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ ላሉ እቃዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ቫት ተመዝጋቢ ያልሆኑ ድርጅቶች በድርጅታቸው ስም የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ያላቸው ሊሆን ይገባል፡፡
- ተጫራቾች ዋናውን እና ኮፒ የመጫረቻ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ሌሎች በጨረታ ሰነዱ ያልተገለጹ ጉዳዮች በግዥ መመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-320-62-06 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
በአብክመ አካ/ደ/ጥ/ል/ባ