በደቡብ ጎንደር ዞን በነፋስ መውጫ ከተማ/አስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት የግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን በCIP በጀት የነፋስ መውጫ ከተማ አስ/ከ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ጽ/ቤት ለሚያሰራው የተለያዩ መሰረተ ልማቶች እና የጽህፈት መሳሪያ ግዥ ሎት 1 የጠጠር መንገድ ግንባታ ቀበሌ 01 ከጌታቸው ጥሩነህ ቤት እስከ እ/ባዩሽ አበራ ቤት ድረስ ፣ሎት 1 የኮብል መንገድ ቀበሌ 04 ከታከለ ፍሌ ቤት እስከ ስላሴ ቤ/ክርስቲያን ድረስ እና ሎት 1 በCIP በጀት የጽህፈት መሳሪያ ግዥ ለመፈጸም እና ለግንባታ ሥራዎቹ የተጫራቾች ደረጃ GC ፣RC ደረጃ 6 እና በላይ የግንባታ ፈቃድ ካላቸው ተጫራቾች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ወይም ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ የሚያቀርቡ፡፡
- ተጫራቾች የግንባታ ብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ የምስክር ወረቀት የታደሰ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-4 የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የተጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ ለሎት 1 የጠጠር መንገድ 300,000.00 /ሶስት መቶ ሽህ ብር ፣ለሎት 1 የኮብል መንገድ ሥራ 120,000.00 /አንድ መቶ ሃያ ሽህ ብር/ እና ለጽህፈት መሳሪያ ለሎት 1 ብር 3,500.00 /ሶስት ሽህ አምስት መቶ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ/1 በመቁረጥ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውንና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በሁለት ፖስታ በማሸግ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ማስገባት አለባቸው ፊርማ ፣ሙሉ ስም ፣የድርጅቱን ማህተም ፣የተጫረቱበትን የሥራ ዓይነት ከፖስታው ላይ አድራሻቸውን በመፃፍ በነ/መ/ከ/አስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት በግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 6 ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 4 በአካል በመቅረብ የማይመለስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነዶች ማለትም /ሎት/ ለግንባታ ስራዎች 500.00 /አምስት መቶ ብር/ እና ለጽህፈት መሳሪያ እቃዎች ግዥ 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ለግንባታ ግዥ ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ማታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይዘጋና በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት የሚያግድ ነገር የለም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን /ካላንደር/ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ለጽህፈት መሳሪያ ግዥ ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ማታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይዘጋና በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት የሚያግድ ነገር የለም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን /ካላንደር/ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻል ማድረግ አይችሉም ጨረታውን ለማዛባት ወይም ለማጭበርበር የሚሞክር ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያው ይወረስና ለወደፊቱ በማንኛውም ጨረታ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
- ጨረታው የሚለየው በሎት /በጥቅል ዋጋ/ በመሆኑ ዋጋውን ሲሞሉ ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም፡፡
- የሚሰሩ ሥራዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታውን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ ፈጽሞ የተከለከለ ነው ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
- በአንዱ ዋጋ እና በጠቅላላ ዋጋው መካከል የዋጋ ልዩነት ቢኖር የአንዱ ዋጋ ገዥ ይሆናል፡፡
- በጥቃቅን የተደራጁ ተጫራቾች ከሆኑ የልዩ አስተያየት ተጠቃሚ የሚያደርጋቸውን የድጋፍ ደብዳቤ ለጽ/ቤቱ በአድራሻ የተጻፈ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አንድ ተጫራች ከአንድ የጨረታ ሰነድ ውጭ መግዛት አይፈቀድም፡፡
- በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው ቁጥር 1/2003 እና በመሻሻያዎቹ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 445 13 74 ወይም 058 445 02 58 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት