በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር በ2017 ዓ.ም በመደበኛ በጀት ማስፈፀሚያ ሎት 1∙ፅህፈት ማሳሪያዎች ፣ሎት 2∙ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3∙ ፈርኒቸር፣ ሎት 4∙ የመኪና ጭነት የትራንስፖርት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና አገልግሎት መጠቀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ) ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ለሎት 4 ለመኪና ጭነት የትራንስፖርት አገልግሎት ተጫራቶች የተሸከርካሪ ማረጋገጫ ሊብሬ እና የባለቤትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ለሎት 1፣2፣3 ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 ለሎት 4 ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት በማይመለስ 00 (ሁለት መቶ ) ብር በኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሂሳብ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ላይ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳሩበት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የገንዘብ መጠን አንድ ፐርሰንት እና ከዚያ በላይ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (cpo) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በግዥ እና ንብረት አስተዳደር ስም በመክፈል የተከፈለበትን ደረሰኝ ከሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ አሸገዉ ኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ላይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለተከታታይ 15/አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱ ክፍት ሆኖ ይቆያል ጨረታው በ 16 ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ላይ በ 16 ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ታሽጐ በዚሁ ቀን በ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- የእቃ እርክክብ ቦታ የሚደረገው ኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ይሆናል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ለውል ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 10 ፐርሰንት በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የተጫራቾች መመሪያ እና የእቃው ዝርዝር መግለጫ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተያይዘዋል፡፡
- በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቁጥር 5 ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት፣ ወይም በስልክ ቁጥር 09-00-41-59-24 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት