ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
94

በላይ አር/በልማት በር መሰናዶ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለቤተ ንባብ አገልግሎት የሚውሉ የመቀመጫ ወንበር እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ቁሳቁሶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ ፡፡

  1. ህጋዊ ፍቃድ ያለውና የ2016 ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. ተጫራቾች በወረዳው የላይ/አ/ወ/ል/ከፍ/መሠ/2ኛ/ደ/ት/ቤት ከገንዘብ ያዥ ቢሮ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 150 /አንድ መቶ ሃምሳ/ ብር ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱን ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ዋናውንና ቅጁ ተለይቶ በ2 ኮፒ ታሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት ሰነዱን በወረዳው የላይ አ/ወ/ል/ከፍ/ትም/ት/መሠ/2ኛ/ደ/ት/ቤት ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበራያ የሚወዳደሩበት ገንዘብ አንድ በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በጨረታ መክፈቻ ዕለት በፖስታው ውስጥ ታሽጎ ማቅረብ አለባቸው፣ ሌተርኦፍ ክሬዲት ከሆነ ፀንቶ መቆያ ጊዜው ዘጠና ቀንና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፣ የጨረታ ሰነዱን ስርዝ ድልዝ ካለበት እና ስለመሰረዙ ልዩ ፊርማ ከሌለበት ውድቅ ይደረጋል፡፡
  8. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ ቀን ከጧቱ 3፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡00  ላይ ይከፈታል፡፡
  9. ጨረታ አሸናፊው  የሚለየው በሎት ወይም በጠቅላላ ድምር ዋጋ ነው፡፡
  10. ተጫራቾች በሚያቀርቡት መወዳደሪያ ሰነድ ስማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
  11. አሸናፊው  ንብረቱን ከት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማስገባት አለበት፡፡
  12. አሸናፊው ተጫራች ኦሪጂናል ያልሆነ እቃ ቢያቀርብ ውሉ የሚሰረዝ መሆኑ እና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ የሚወረስ መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡
  13. ጨረታው ሙሉ ወጪውን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  14. ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልገው በስልክ ቁጥራችን 09 18 80 57 58 ወይም 058 116 0718 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
  15. አሸናፊው  በፍትህ ውል የሚወስድ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
  16. ማሳሰቢያ፡- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የልማት በር መሰናዶ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here