የበዓል ወቅት ጥንቃቄ

0
118

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን መጪዎቹን በዓላት በሰላም ተከብረው እንዲጠናቀቁ ኅብረተሰቡ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመሆን ሕገ ወጥ ድርጊቶችን አስቀድሞ እንዲከላከል አሳስቧል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ረዳት ኮሚሽነር መሠረት ደባልቄ በክልሉ የሐሰተኛ የብር ኖት ዝውውር የወንጀል ተግባር በተደጋጋሚ ተከስቷል ብለዋል።

የጸጥታ ኃይሉ ኅብረተሰቡን ግንዛቤ ከማስጨበጥ ባለፈ የወንጀሉን ፈጻሚዎች ተከታትሎ በቁጥጥር ሥር እያዋለ እንደሆነም ለአሚኮ ገልጸዋል።

ባለፈው ሩብ ዓመት “ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ የሐሰተኛ የብር ኖት ሲዘዋወር ተይዟል”ም ነው ያሉት ረዳት ኮሚሽነሯ።

የሐሰተኛ የብር ኖት በክልሉ በሁሉም ቦታዎች እንደሚዘዋወር የጠቆሙት ኮሚሽነሯ በተለይ በባሕር ዳር ከተማ፣ በአዊ እና በዋግ ኽምራ በከፍተኛ መጠን የሐሰተኛ የብር ኖት ዝውውር ተከስቷል፤ በቁጥጥር ሥርም ውሏል ብለዋል።

አርሶ አደሩ እና የንግዱ ማኅበረሰብ በስፋት ግብይት በሚያደርግበት የበዓላት ወቅት ወንጀል ፈጻሚዎች የሐሰት የብር ኖት አሳትመው በመዘዋወር ነዋሪውን ለኪሳራ ይዳርጋሉ፤ ሰላማዊውን ገበያም ያውካሉ ብለዋል።

ይህም ከግለሰብ ባለፈ የሀገርን ምጣኔ ሀብት እና ገጽታ ይጎዳል ነው ያሉት።

የወንጀል ፈጻሚዎች በተለይ በበዓል ሰሞን የእርድ እንስሳት ወደ ገበያ መውጣታቸውን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ሐሰተኛ የብር ኖት በሥፋት ሊያዘዋውሩ ስለሚችል ኅብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግም ረዳት ኮሚሽነር መሠረት አሳስበዋል።

(ማራኪ ሰውነት)

በኲር የታኅሳስ 28  ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here