ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
103

የፍኖተሰላም ከተማ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚዉል የተለያዩ ዕቃዎችን ማለትም ሎት 1 ቧንቧና መገጣጠሚያ፣ ሎት 2 የቧንቧ መፍቻዎችና የስራ መሳሪያዎች፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣ ሎት 4 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 5 የውሃ ጥራት ኬሚካል ኤጀንት፣ ሎት 6 የደንብ ልብስ የተዘጋጁ ልብሶች፣ ሎት 7 የደንብ ልብስ ጫማ ፣ሎት 8 የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ ፣ሎት 9 ኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና ሎት 10 የኦዲት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የግዥ ዘዴ ከዚህ በታች የተዘረዘሩመስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት፡-
1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
3. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉ፡፡
5. የግዥዉ መጠን ከ200‚000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ለሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ የተመዘገቡ መሆናችን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
6. የተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ብር አንድ ከመቶ ከ1-9 ለተዘረዘሩ እቃዎች ሲሆን ለኦዲት አገልግሎት ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በዉሃ አገልግሎቱ ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
7. ተጫራቾች ከ1-5 የተዘረዘሩትን ማሰረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
8. የጨረታ ማስታወቂያዉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይዉላል፡፡ በ15ኛዉ ቀን 11፡30 ሳጥኑ ይታሸጋል በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም ጨረታዉ በግልጽ ይከፈታል፡፡
9. ማንኛዉም ተጫራች ሀሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ቢሮ ቁጥር አራት /4/ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
10. በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማስገባት አይቻልም፡፡
11. የጨረታ መክፈቻዉ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
12. በጨረታዉ ለተሸነፉ ተጫራቾች ከአሸናፊዉ ጋር ዉል እንደተያዘ የጨረታ ማስከበሪያዉ ይመለሳል፡፡
13. ተጫራቾች የማይመለስ ብር ለእያንዳንዳቸው 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 2 ዘወትር በሥራ ሰዓት መዉሰድ ይችላሉ፡፡
14. አሸናፊዉ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ያሸነፉበትን የሎት ዕቃዎች ጠ/ዋጋ የዉል ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /በጥሬ ገንዘብ/ ለፍኖተ ሰላም ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገ/ጽ/ቤት አስይዘዉ ዉል በመፈጸም ያሸነፉትን ዕቃ ፍ/ሠ/ከ/ዉ/ፍ/አገ/ጽ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸዉ፡፡
15. ተመሳሳይ የሆኑ እቃዎች በአንድ ምድብ /ሎት/ በማድረግ ዉድድሩ የሚገለጸዉ በጠቅላላ የድምር ዉጤት ነዉ፡፡
16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ /በከፊል/ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
17. በጨረታዉ መሰረዝ ምክንያት ተጫራቾች ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነትን አይወስድም::
18. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 775 13 87 /00 75 /09 23 42 61 23 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የፍኖተሠላም ከተማ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here