ሜዴክስ ዲያግኖስቲክስ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስር ከሚተዳደሩት የመንግስት የልማት ድርጅት አንዱ የሆነው የንጋት ኮርፖሬት አካል ሲሆን ፤በክልሉ የሚገኘውን የጤና አገልግሎት ጥራት ማሻሻል ተቀዳሚ ተግባሩ ነው፡፡ ይህን መሠረት በማድረግ መድሀኒት ከውጭ ለማስገባት ባወጣው ኢምፖርት ፈቃድ ቁጥር 13132/MEMDICER/2024 መሰረት ከሀገር ውስጥ የመድሃኒት እና የላቦራቶሪ ግብአት አምራች ድርጅቶች /ፋብሪካዎች/ ጋር ለ2017 ዓ/ም በጀት አመት ለ1 አመት የሚቆይ ውል ይዞ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ድርጅቶች /አምራች ፋብሪካዎች/ የሚያመርቱትን መድሃኒት በአይነት፣ በመጠን እና በግራም በመግለፅ የሚያቀርቡበትን /መሸጫ ዋጋ/ በተጨማሪም ለዚሁ ግብአት የትራንስፖርት አገልግሎት የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ባህርዳር ድረስ ለማድረስ አገልግሎቱን የሚሰጡበትን ዋጋ አካትተው በዝርዝር እንዲያቀርቡ ይጠበቃል፡፡
- ዋጋ ሞልተው ሲያቀርቡ የመድሃኒት አምራች መሆናቸውን የሚገልፅ EFDA ሰርትፍኬት እና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ አይይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ይቆያል ፡፡
- የጨረታው ሰነድ ከጥር 30/2017 ከጠዋቱ 4፡00 ጨረታው በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት፣ የባ/ዳር ተወካዮች በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- የግብር ከፋይ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ቲኦቲ እና የቫት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች የቴክኒካል ፕሮፖዛል፣የዋጋ ማቅረቢያ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በሰም በታሸገ ኢንቮሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ሲኘኦ በባንክ ሁለት በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ሰነዱን የሚያቀርቡበት መንገድ በአካል ወይም በፖስታ ቁጥር 1555 ስ/ቁ 058 320 6668/058 320 70 68 መደወል ይችላሉ፡፡ - አድራሻ ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 ኖክ አካባቢ ሪየስ ኢንጅነሪንግ ህንፃ 2ኛ ፎቅ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
ሜዴክስ ዲያግኖስቲክስ