ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
83

በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ተኝተው ለሚታከሙ ታካሚዎች  አገልግሎት የሚዉል ኦክስጅን ሲሊንደር አስሞልቶ ለማምጣት የጭነት የመኪና ኪራይ ባህር ዳር ደርሶ መልስ ጭኖ ለማምጣት እና መድሀኒት ከጎንደር ወደ መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል  ለማምጣት  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት  ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  2. የቫት ተመዚጋቢ የሆኑ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የመኪናውን ሊብሪ (የባለቤትነት ማረጋገጫ) ፎቶ ኮፒ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  5. ለጨረታ የሚቀርበው ተሸከርካሪ ለደረቅ ጭነት አገልግሎት የሚውል መሆኑን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ኦክስጅን ሲሊንደር ያልተሞላውን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ጭኖ ባህር ዳር ኦክስጅን ማምረቻ አስሞልቶ መተማ ሆስፒታል ማምጣት የሚችል፡፡
  7. የመድን ኢንሹራንስ ውል ያለው እና ኮፒውን ማስያዝ የሚችል፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ስዓት በመተማ ሆስፒታል ግዥ እና ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ወይም ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ  ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘውትር በሥራ ሰዓት ጨረታውን  በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ከ 05/05/2017 እስከ 19/05/2017 ዓ.ም ቀን ጀምሮ መውሰድ እና መመለስ የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ማለትም በ 20/05/2017  ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል  ግዥ እና ፋይናንስ ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. የጨረታ ሰነዱ ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ የሌለው እና በሰነዱ ላይ ስም እና ፊርማ እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም መቀመጥ አለበት፡፡
  11. ስለጨረታው ዝርዘር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 331 01 74 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
  12. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጭነት ዋጋ  አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው ወይም በጥሬው ማስያዝ ይችላሉ፡፡
  13. አሸናፊው ድርጅት መ/ቤቱ እንዲጫን በሚጠየቅበት ሰዓት በአስቸኳይ ማምጣት የሚችል መሆን አለበት፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- ኦክስጅን ሲሊንደር ከመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል  ባህርዳር ጭኖ አስሞልቶ ለማምጣት በሚኔደበት ቀን  በመብራት መጥፋት ምክኒያት ወይም በወረፋ ምክኒያት ቢዘገይ ወረፋውን ጠብቆ አስሞልቶ መምጣት የሚችል  መሆን አለበት፡፡

የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here