በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2017 ዓ.ም በጀት አመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚዉል ሎት 01 የኤሌክትሮኒክስ እቃ ፣ሎት 2 ፈርኒቸር እንዲሁም ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና በግልጽ ጨረታ አዳድሮ ለመግዛት እና ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እና የሚጠገኑ እቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 50.00 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ስዓት በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ እና ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ወይም ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የእቃው ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ ባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው ወይም በጥሪው ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታውን በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ከ 05/05/2017 እስከ 19/05/2017 ዓ.ም ጀምሮ መውሰድ እና መመለስ የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ማለትም በ 20/05/2017 ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ እና ፋይናንስ ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት በጥቅል እቃ ዋጋ ሲሆን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በነጠላ ዋጋ አሸናፊ መለየት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊ ድርጅቱ በምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትህ መምርያ ቀርቦ ውል መውሰድ የሚችልና እቃዎችን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ባለው ንብረት መጋዘን በዝርዝር ማስረከብ የሚችል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 331 03 54 /058 331 01 75 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው እቃውን ማቅረብ ያለበት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰጠውን ሞዴል እንጂ ሥርዝ /ድልዝ ሌላ ተመሳሳይ እቃ ማቅረብ አይችልም፡፡
- መ/ቤቱ ከተጠየቀው ጠቅላላ እቃ አቅረቦት ሃያ በመቶ ከፍ ወይም ዝቅ ማለት ይችላል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል