በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለ4ቱም ፑል መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1 ጽ/መሳሪያ ፣ሎት 2 የጽዳት እቃ ፣ሎት 3 ቋሚ አላቂ ፣ሎት 4 ፖሊቲን ቲዩብ እና ሎት 5 ኮድ LN-166 የመኪና እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- እቃው ወይም የአገልግሎት ግዥ መጠን 200,000.00 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የጨረታ ሰነዶች ግልጽና የሚነበቡ መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለየአንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ለመክፈል ከተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 1 ጽ/መሳሪያ 17,000.00 ፣ሎት 2 የጽዳት እቃ 3,000.00 ፣ሎት 3 ቋሚ አላቂ 4,000.00 ፣ሎት 4 ፖሊቲን ቲዩብ ብር 3000.00 ፣ሎት 5 ኮድ 166 የመኪና እቃ 10,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ /ቢድ ቦንድ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ05/52017 እስከ 19/05/2017 11.30 ደረስ ጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ20/05/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱ ላይ የአንድ ዋጋ ሥርዝ ድልዝ ከሆነ ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት (በድምር ዋጋ ነው)፡፡ በሰነዱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡ አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች መ/ቤቱ በጠየቀው ስፔስፊኬሽን መሰረት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ሲነፃጸር የተጋነነ ከሆነ ጨረታው ውድቅ ይሆናል፡፡
- ሁሉም የሚቀርቡ እቃዎች ጥራታቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት እቃዎችን ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሱ አጓጉዞ በማቅረብ ንብረቱን በየንብረት ክፍል አስረክቦ ገንዘቡን ወጭ አድርጎ ይወስዳል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ሆኖ ወደፊትም በመንግስት ጨረታ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል የማይችል ሲሆን በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን ዋጋና መግለጫ ማሻሻል አይችልም፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 222 00 12 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት