ግልጽ የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
92

በአፈ/ከሳሽ ዘመን ኢትዮጵያ አስመጭና ላኪ በአፈ/ተከሳሽ 1ኛ. አቶ ታደሰ ስመኝ 2ኛ.ወ/ሮ ሀብታም ወንድምአገኝ ጀንበሬ መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በዱርቤቴ ከተማ ቀበሌ 02 በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ መንገድ ፣በሰሜን የማንደፍሮ ይዞታ፣ በደቡብ መንገድ መካከል ተዋስኖ የሚገኘውን 2800 ካ/ሜትር ለሞቴል አገልግሎት የሚውል ከብሎኬት የተሰራ አራት ክፍል የንግድ ቤት እና ለነዳጅ ማጠራቀሚያ የሚውል መሬት ውስጥ የተቀበሩ እያንዳንዳቸው 50,000 (አምሳ ሽህ ሊትር) ነዳጅ የሚይዙ 4 ታንከሮችን ከማስተላለፊያ ቱቦዎች ጋር በዜሮ መነሻ ዋጋ የካቲት 06/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 በግልጽ ጨረታ ይሸጣል፡፡ ስለሆነም  መጫረት የምትፈልጉ ሁሉ ጨረታው በሚካሄድበት ለዱርቤቴ ከተማ ቀበሌ 02 ወይም ንብረቱ በሚገኝበት በመገኘት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በዕለቱ ጨረታውን ያሸነፈ ያሸነፈበትን 1/4ኛውን በሞ/85 ጨረታው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ የሚያዝ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here