ዳንግላ ከተማ አስተዳደር ከ/ል/መ/ል/ጽ/ቤት የመሬት ልማት ባንክ ቡድን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ መሠረት ለመኖሪያ እና ለንግድ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን 1ኛ/ዙር በግልጽ መደበኛ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ከ05/05/2017 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር ለድርጅት ሆነ ለመኖሪያ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ዳንግላ ከተማ አስ/ከ/ል/መ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በመምጣት ዘወትር በሥራ ስዓት ሰነድ መግዛት እና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሣውቃለን፡፡ የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ እና መሸጫ ጊዜ ከ05/05/2017 ዓ/ም እስከ ጥር 14/05/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው ጥር 14/05/2017 ዓ.ም ከቀኑ በ11፡00 ሁሉም የጨረታ አስፈፃሚ ቡድን አባላት እና አግባብ ያለው አካል የሚሰይማቸውን ታዛቢዎች በተገኙበት ይሆናል፡፡
- ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለፀው መርሃ ግብር መሠረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ጥር 15/2017 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአገው ምድር አዳራሽ ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በዳንግላ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ቦታዎች በሚለጠፋ ማስታወቂያዎች እና ቢሮ ቁጥር 6 ወይም በስልክ ቁጥር 058 221 00 54 ወይም 058 221 00 06 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ዳንግላ ከተማ አስተዳደር ከ/ል/መ/ል/ጽ/ቤት