በደቡብ ጎንደር ዞን የመካነ ኢየሱስ /ከ/አስ/ገን/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት የግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን መሪ የተለያዩ ግዥዎችን ሎት1.የጽህፈት መሳሪያ፣ሎት2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ሎት3. የፈርኒቸር እቃዎችን ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት የገንዘብ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ሰትርቲፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር00/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከመ/ኢ/ከ/አስ/ገ/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 22 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የእቃውን ዝርዝር መግለጫዎች /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል፡፡
- ሎት3 በሚቀርበው ናሙና ከተቋማችን ላይ ይገኛል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚሞላው ዋጋ ማንኛውንም ግብር ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደርበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱ ላይ እና ፖስታው ላይ የንግድ ድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ማድረግ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን ባንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ /ኢንቨሎፕ/ መ/ኢ/ከ/አስ/ገ/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 22 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባትይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ16ኛውቀን ሎት ከጧቱ 2፡30 ታሽጎ 3፡00 ይከፈታል ፤ሎት2. እና ሎት 3. ከጧቱ 2፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል ፤ማንኛውም ተጫራች በ16ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ እስከሚዘጋበት ስዓት ድረስ ጨረታውን ማስገባት ይችላል፡፡ ለሁሉም ሎቶች ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው የሚከፈት ሲሆን የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም የበአል ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በዝርዝር ወይም በሎት ከቀረቡት እቃዎች ውስጥ ዋጋው ነጥሎ መሙላት አይችልም፡፡ ነጥሎ የሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው እንደተቋሙ ፍላጎት በጥቅል ወይም በተናጠል ሊለይ ይችላል፡፡
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን እቃ በሙሉ በራሱ ወጭ በማጓጓዝ ከገዥው ተቋም ድረስ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊ ከሆነው ተጫራች ላይ 2በመቶ ከተከፋይ ሂሳብ ግብር/ ዊዝ ሆልድ/ ተቀናሽ ይሆናል፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርቦ የውል ማስከበሪያ 10በመቶ በማስያዝ ውሉን መፈጸም ይኖረበታል፡፡ በተባለው ቀን መጥቶ ውሉን የማይፈፅም ከሆነ ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያው ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡ ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0584470121 እና 0584471022 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የመካነ ኢየሱስ ገንዝብ አካባቢኢኮኖሚልማትጽ/ቤት