ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
101

የጨረታ ቁጥር ARARI 02/05/2017

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የጽህፈትና የጽዳት ዕቃዎች በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ 25.00 /ሃያ አምስት ብር/ በመክፈል አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 119 በግንባር በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ተያይዟል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ለጽህፈት መሳሪያ 6000.00 /ስድስት ሽህ ብር/፣ ለጽዳት ዕቃዎች 3000.00 /ሦስት ሽህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው ፤በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ቢሮ ቁጥር 119 ደረሰኝ በማስቆረጥ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 120 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን ጠዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፤16ኛው ቀን የሚውለው በበዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጠዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ኦፊሰሮች ክፍል ቢሮ ቁጥር 120 በ16ኛው ቀን ጠዋቱ በ3፡30 ተዘግቶ 4፡00 ላይ ይከፈታል ፤16ኛው ቀን በበዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጠዋቱ በ3፡30 ተዘግቶ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች በጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ያሸነፉበትን አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 120 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 60 77 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 50 74 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here