ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
93

ቁጥር – 001/2017

የሰሜን ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ የግብዓት ገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ቡድን ለ2017//2018 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውሉ የዳፕ እና ዩሪያ በድምሩ 1,247,232/አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ አርባ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ ሁለት / ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በመርከብ ዩኒየን በስሩ ባሉ 75 መሠረታዊ ማኅበራት መጋዘን ድረስ ለማጓጓዘ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርት ደርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ውል ከተፈፀመበት ቀን  እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ባለው  ጊዜ የሚቆይ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል። ስለዚህ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር /ገበያ ልማት ሚኒስቴር/ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. በጨረታው የሚሣተፉ ተጫራቾች ከ70 ኩንታል በላይ የሚጭኑ ተሽከሪካሪዎች የሚያቀርቡ ከሆነ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. እንዲሁም ተጫራቾች የሚያቀርቡት ከ70ኩንታል በታች ከሆነ በክልል ትራንስፖርት ቢሮ ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የተሽከርካሪ ዝርዝር /ተ.ቁ ፣የሴሌዳ ቁጥር፣የመኪናው ዓይነትና የመጫን አቅም /የሚያስረዳ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ወይም ከክልል መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የተሰጠ የ2017 ዓ.ም ወቅታዊ የታደሠ ምዝገባ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ 1 እስከ 5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የሚጓጓዘውን የአፈር ማዳበሪያ አይነት፣ መጠን ርቀት በኪሎ ሜትር ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ/ በመክፈል ሰ/ጎጃ/ዞን ገንዘብ መምሪያ  ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይቻላል፡፡
  8. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በሚወዳደሩበት መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማህበራት ዩኒየን ስም ማስያዝ አለባቸው።
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን በአንድ ፖስታ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በማሸግ በአብክመ ግብርና ቢሮ የሰሜን ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ በግብ/ግብአት ገጠር ፋይናንሰ አቅ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 313/311 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ማለትም 4፡00  ሠነዱን በሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈተው በእለቱ  በ4፡30 በመምሪያዉ  በሚዘጋጅ ቦታ ይከፈታል፡፡
  10. መምሪያዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ መምሪያዉ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0912764243/0923899289 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የሰሜን ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here