በምዕራብ ጎጃም ዞን የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ /ዩኒዬን ኃ.የተ. ማህበር የ2017 ዓ.ም በጀት አገልግሎት የሚሰጡ ሎት1. የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ ሎት2. የተለያዩ የመኪና ጎማዎች ፣ሎት3. ህትመት ፣ ሎት.4 የተዘጋጁ አልባሳት፣ ሎት5. የዱቄት ፋብሪካ መለዋወጫዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፍ የታደሰ የንግድ የስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
- የግዥው መጠኑ ከብር 200.000 /ሁለት መቶ ሽህ/ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ/ ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ከላይከ 1-3 የተዘረዘሩትን የምታሟሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 8 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ስዓት ቅዳሜን ጨምሮ የማይመለስ ብር 00/ሀምሳ /ብር በመክፈል ከዩኒየኑ ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 1 /ሂሳብ ክፍል/ እስከ 8፡ 00 ድረስ መውሰድ ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ነገር ግን ማንኛውም ተጫራች በሙሉ ዝርዝር ላይ በእያንዳንዱ ዋጋ መሙላት ይኖርበታል፡፡፡-
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን/ ካላንደር/ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተጠቀሰው ስዓት ይከፈታል፡፡
- የንግድ ፍቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እንዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጐልም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት ጥቅል ድምር ነው፡፡
- አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር 10በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡ይህ ካልሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
- የማስረከቢያ ቦታ ዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየንኃ. የተቡሬ ከሚገኘው ጽ/ቤት ድረስ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40/1032 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡
የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ /ዩኒዬን ኃ.የተ.የ.ማህበር