ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
84

በሰሜን ጎንደር ዞን በጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. ኤሌክትሮኒክስ ፣ሎት 2. ናፍጣ ትራንስፖርት ፣ሎት 3. የመኪና ዘይትና ቅባት ፣ሎት 4. የጽዳት እቃዎች ፣ሎት 5. እስፖንጅ ፍራሽ እና ሎት 6. የመኪና መለዋወጫ እቃዎች  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ጽ/ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፍል፡፡ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-

  1. በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ  ኮፒ ማቅረብ  ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. ለተጨማሪ ሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢዎች የተጨማሪ ሴት ታክስ ማረጋገጫቸውን ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. በእያንዳንዱ ሎት የዕቃዎቹን አይነትና ዝርዝር መገለጫ /ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት  ቢሮ ቁጥር 11  ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አንድ ነጥብ አምስት በመቶ በእያንዳንዱ ሎት ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በሁኔታው ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ-1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው በአየር ላይ ከ 12/05/2017 ዓ.ም እስከ 26/05/2017 ዓ.ም ድረስ ይውላል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ቀናት ከ12/05/2017 ዓ.ም እስከ 26/05/2017 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይቻላል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጃ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን 27/05/2017 ዓ.ም 9፡00  ታሽጎ 9፡15  ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኝም ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡
  11. ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር /በሎት/ ድምር ይሆናል፡፡
  12. ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ፓራፍ ይደረግበት፡፡
  13. ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመው ጥራታቸው በባለሙያ ሲረጋገጥ ነው፡፡
  16. ተጫራቾች ሎት 6 የመኪና መለዋወጫ እቃ የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመው ጥራታችው በባለሙያ እየተረጋገጠ ማ/ጎንደር ዞን ጎንደር ከተማ ከሻጭ መጋዝን ነው፡፡
  17. ተጫራቾች ከሎት 1-5 ድረስ ያሎት የእቃዎቹን ርክክብ ጃናሞራ ወረዳ መካነ-ብርሃን ከተማ ንብረት ክፍል ድረስ አምጥተው የሚያስረክቡ ሲሆን ትራስፖርትን እንዲሁም ማውረጃና መጫኛ አስበው መሙላት አለባቸው፡፡
  18. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.10 በአካል በመገኘት ወይም በስቁ. 058 294 00 23/ በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ  ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here