ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
85

የስማዳ ወረዳ ፍርድ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለፍርድ ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ ፣ሎት 2 ህትመት እና ሎት 3 ፈርኒቸር የቢሮ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በእያንዳንዱ ዘርፍ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ነጋዴዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆንና ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ እቃዎችና አገልግሎቶች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ከላይ ለተጠቀሱት የአገልግሎት00 /ሃያ ብር/ በመክፈል ስ/ወ/ፍ/ቤት/ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በጥሬ ገንዘብ በዋና ገንዘብ ያዥ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በማስያዝ የስያዙበትን ኮፒ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ ዋስትና አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በስማዳ ወረዳ ፍርድ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 09 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘውትር በሥራ ስዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖረባቸዋል፡፡
  10. በጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ/ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግ/ፋ/ን/ አሰ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 09 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል፡፡
  11. ፍ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 09 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 64 66 02 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. ርክክቡ የሚፈጸምበት ቦታ በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ስማዳ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው፡፡
  14. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  15. ፍ/ቤቱ በአንድ ሰነድ/ የተዘረዘሩትን ተመሳሳይ እቃዎች ከፋፍሎ መጫረት አይቻልም፡፡
  16. ፍ/ቤቱ በአንድ ሰነድ በአንድ ምድብ /ሎት/ የተዘረዘሩትን ተመሳሳይ እቃዎች ተጫራቹ በሞላው ዋጋ የጨረታ ሰነድ አሸናፊው የሚለየው በጠቅል ዋጋ ነው፡፡

የስማዳ ወረዳ ፍርድ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here