ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
93

በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የጣና ክ/ከተማ አስተዳደር ለሚያስገነባው G+2+T የአስተዳደር ህንፃ part A&B የመሰረትና የG+0 ኮለመን ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ የህንፃ ተቋራጮች መወዳደር የምችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. በዘርፉ አግባብነት ያለዉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይነት መለያ   ያላቸው፡፡
  2. ደረጃ 5 እና በላይ በህንፃ ሥራ ተቋራጭነት ወይም በጠቅላላ ሥራ ተቋራጭነት ፈቃድ ያላቸው፡፡
  3. ከታወቀ ተቋም ወይም መ/ቤት በህንፃ ግንባታ ሥራ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከለይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ዋናውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚሰራውን የግንባታ ሥራ ቢል ኦፍ ኳንቲቲ /ስፔስፊኬሽን/ እና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. የግንባታ ጥሬ እቃ ማለትም ሲሚንቶ፣ የአርማታ ብረት፣ አሸዋ፣ ጠጠርና ድንጋይ በጽ/ቤቱ የሚሸፈኑ ሲሆን በአላቂ የግንባታ ግብዓቶች እንደ ሚስማር ፣ አጣና እንጨት /ክርስቲ/ ፣ፎርም ወርክ/ እንዲሁም ውሃ ማጠጣት ፣ የሰው ሃይል/ የባለሙያ/ ፣ማሽነሪና አስፈላጊ መሣሪያዎች እና ሌሎችም ቁሣቁሶች በተጫራቹ የሚሸፈኑ ይሆናል፡፡
  7. የግንባታ አሸናፊ ድርጅቱ ማሽነፉ  በተገለፀ በ5 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል በመያዝ ውል ከያዘበት በ15  ተከታታይ ቀናት ውስጥ ወደ ሥራ መግባት የሚችል መሆን አለበት፡፡
  8. የጣና ክ/ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ሰነዱን የማይመለስ 1000.00 /አንድ ሽህ ብር/ በመክፈል መግዛትና መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት አምስት በመቶ ወይም የጠቅላላ ዋጋውን አምስት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የጣና ክ/ከተማ አስተዳደር በሚል ስም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ይህን መመዘኛ የምታሟሉና መወደደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከቀን 12/05/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ21 ቀን በአየር ላይ በመዋል በ21 ኛዉ ቀን ከቀኑ 11፡00 ጨረታዉ ተዘግቶ በ22ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 3፡30  በጣና ክፍለ ከተማ የግዥ ፋይናንስ ቢሮ ጨረታዉ  ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡

የጣና ክ/ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here