ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
83

በሰሜን ጎጃም ዞን በአዴ ከተማ አስተዳደር የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል በ2017 በጀት ዓመት  ከዚህ በታች የተገለፁትን ሎት1. የግብርና፣ ሎት 2. የኤሌክትሮኒክስ ፣ሎት 3. የፅህፈት መሳሪያዎች ፣ሎት. የጽዳት እቃዎች፣ሎት5. ኬሚካል፣ሎት6 .የላብራቶሪ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ  የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የግዥው መጠን ከብር200000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር / እና በላይ ከሆነ

የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ

የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን

ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻችው ጋር አያይዘው በፖስታ በማሸግ በማዕከሉ

የጨረታ  ሳጥን  ማስገባት አለባቸው፡፡

  1. የዕቃውን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን)  ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100.0 /አንድ መቶ/ ብር በመክፈል ከግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 3 ማግኘት ይቻላል፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት እቃ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት

በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡

  1. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ

የተጠበቀ ነው ።

  1. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል። በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00  ታሸጎ በዚሁ ቀን 4፡30 በማዕከሉ አዳራሽ ይከፈታል። 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ይከፈታል፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ የተወዳዳሪው ስም አድራሻ የሚመለከተው (ህጋዊ

ወኪል ) የተፈረመበት የተሟላና ማህተም ያረፈበት መሆኑን አረጋግጦ ማቅረብ አለባቸው።

  1. በዘርፉ እንዲወዳደሩ የሚያስችል የንግድ ፈቃድ ካላቸው ከአንድ በላይ ሎት መወዳደር ይችላሉ፡፡
  2. አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው ከአምስት የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10በመቶ በሲፒኦ በማስያዝ ውል መፈፀም ያለባቸው ሲሆን ተጫራቹ አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች ሙሉ በሙሉ ማዕከሉ ድረስ የመቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  3. ዋጋ ሲሞሉ አሸናፊውን ለመለየት ያመች ዘንድ በአንድ ሎት ለቀረቡ እቃዎች ሙሉ በሙሉ ዋጋ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለበለጠ መረጃ 058-3381166 ደውለው ማግኘት ይችላሉ::

የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here