ፍርድ ቤቶች በቴክኖሎጂ ሊተሳሰሩ መሆኑ ተገለጸ

0
116

ኢትዮ- ቴሌኮም  የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶችን በኔትወርክ የማገናኘት እና የኦዶቪዥዋል ሥራን ለማከናዎን የሚያስችለውን ውል ተፈራርሟል፡፡

የኢትዮ- ቴሌኮም ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ፍሬሕይዎት ታምሩ  ናቸው በባሕር ዳር ከተማ ከሰሞኑ ተገኝተው የሲሲቲቪ ውል እና ሌሎች ሥራዎችን በጋራ ለማከናወን የሚያስችለውን ውል የተፈራረሙት፡፡ ዋና ሥራ አሥፈፃሚዋ እንደ ሀገር ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በተያዘው ዕቅድ መሠረት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የጀመረው የዲጅታላይዜሽን ሥራ ላይ በትብብር ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን የአሚኮ ዘገባ አመላክቷል፡፡

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ዓለምአንተ አግደው  እንዳሉት  የክልሉ ፍርድቤቶች ሥራ በዲጅታላይዜሽን መታገዙ የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ ያደርገዋል። እንደ ኢትዮ – ቴሌኮም ካለ አንጋፋ እና በሀገር ኢኪኖሚ ዕድገት እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሠረታዊ ለውጥ እንዲመጣ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ካለ ተቋም ጋር አብረው በመሥራታቸውም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ ኢትዮ ቴሌኮም በተፈረመው ውል መሠረት በአጭር ጊዜ እና በጥራት አገልግሎቱን እንደሚያቀርብ ያላቸውን ዕምነትም ገልፀዋል፡፡

(ሳባ ሙሉጌታ)

በኲር የጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here