ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
106

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሎት.1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት.2 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ ቲን /ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ምዝገባ ሰርትፊኬት ያላቸዉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በግዥና /ፋ/ን/አስ/ቡድን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ  ለተከታታይ 15 ቀናት ባሉት የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር00 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ/ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ፣በጥሬ ገንዘብ ካስያዙ ከኮሌጁ ገንዘብ ቤት ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ኮፒ ከፖስታዉ ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጠ/ጤ/ሣ/ኮሌጅ በግዥና /ፋ/ን/አስ/ቡድን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 10፡30 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ስዓት ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታዉ በዚህ ዕለት ከቀኑ 10፡30 ታሽጎ በ16ኛዉ ቀን ከጧቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡የመክፈቻ ቀኑ በዓል ወይም ዝግ  ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  8. የዕቃው መለያ ዝርዝር /ሰፔስፊኬሸን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ዉድድሩ የሚካሄደው በሎት ምድብ ነው፡፡
  9. ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ 058-448-0234 ደውለው መጠየቅ ወይም ጠ/ጤ/ሣ/ኮሌጅ በግዥና /ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር-9 በመምጣት መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ስ.ቁ – 058-448-0234 መደወል ይቻላል፡፡

                                                         የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here