ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
84

በአብክመ በደ/ጎ/መ/ዞን በነፋስ መውጫ ከተማ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ፋን/አስ/ቡድን ለነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የመኪና እቃ መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ወይም ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ የሚያቀርቡ፡፡
  3. የግዥ መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-3 የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የተጫረቱበትን 4,000 /አራት ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 በመቁረጥ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውንና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በሁለት ፖስታ በማሸግ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ማስገባት አለባቸው፡፡ ፊርማ ፣ሙሉ ስም ፣የድርጅቱን ማህተም ፤የተጫረቱበትን የሥራ ዓይነት ከፖስታው ላይ አድራሻቸውን በመፃፍ በነ/መ/ከ/አስ/ገ/አ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 6 ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 4 የማይመለስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነዶች /ሎት/ 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይዘጋና በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት የሚያግድ ነገር የለም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን /ካላንደር/ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻል ማድረግ አይችሉም፡፡ ጨረታውን ለማዛባት ወይም ለማጭበርበር የሚሞክር ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያው ይወረስና ለወደፊቱ በማንኛውም ጨረታ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
  10. ጨረታው የሚለየው በሎት /በጥቅል ዋጋ/ በመሆኑ ዋጋውን ሲሞሉ ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም፡፡
  11. የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ጨረታውን ሲሞሉ በነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ ሥርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
  14. በአንዱ ዋጋ እና በጠቅላላ ዋጋው መካከል የዋጋ ልዩነት ቢኖር የአንዱ ዋጋ ገዥ ይሆናል፡፡
  15. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
  16. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 445 13 74 ወይም 058 445 02 58 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here