የላይ ጋይንት ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ 1ኛ. የጽህፈት፣ 2ኛ.የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና 3ኛ. የህትመት ሥራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ማናቸውም ድርጅት ተወይም በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የሚያቀርቡት ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች /ቫት/ ተመዝጋቢ ከሆኑ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚገዙ የእቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሸን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሰነድ 50.00 /ሃምሳ ብር/ የማይመለስ ቢሮ ቁጥር 18 መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም /ቢድ ቦንድ/ በሚወዳደሩበት ብር የሚመለስ ሁለት በመቶ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግዥ እና ፋይናንስ ንብርት አስተዳዳር ቡድን መሪ ወይም ቢሮ ቁጥር 18 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን በተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በሥራ ስዓት ከ19/05/2017 ዓ.ም 03/06/2017 ዓ.ም ከ11፡30 ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በዚህ ቀን 11፡30 በኋላ የጨረታ ስጥኑ ይታሸጋል፡፡ በ15 /በአስራ አምስት / ቀን ውስጥ ካላንደር ካለ በሚቀጥለው ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 18 በ04/06/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 18 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 445 00 38 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የላይ ጋይንት ወረዳ ፍ/ቤት