ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
83

በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር የነፋስ መውጫ /ፖ/ቴ/ ኮሌጅ ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት2. ሕንፃ መሳሪያ፣ሎት3. ኤሌክትሮኒክስ ፣ ሎት4.የግብርና እቃዎችን፣ ሎት5. የሆቴል ማሰልጠኛ እቃዎች ፣ ሎት6. ሶስት ኩንታል የሚመዝን የብር ማስቀመጫ ካዝና መግዛት ይፈልጋል ፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. ህጋዊ ንግድ ፍቃድና /ቲን/ ያላቸው ፎቶ ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00/ ሁለት መቶ ሽህ/ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት መወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸዉ ስልክ ጨምሮ የድርጅታቸውን ማህተም መኖር አለበት፡፡
  5. ጨረታው ከተዘጋጀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ የማይቻልና ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  6. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም በመንግስት መ/ቤት ጨረታ የማይሳተፉ ይሆናሉ፡፡
  7. ጨረታው ከተጫራቾች ውስጥ አሸናፊ የሆነውን ድርጅት በውሉ መሰረት ነፋስ መዉጫ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ድረስ እቃዉን ማስረከብ አለበት፡
  8. ጨረታው ተከፍቶ እንዳበቃ ከአምስት ቀናት በኋላ ለተከታታይ 5 ቀናት ውል ይሰጣል፡፡የውል ማስከበሪያ በመመሪያው መሰረት የዋጋውን 10 በመቶ ይሆናል፡
  9. ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ3፡00 ተዘግቶ በ4፡00 ይከፈታል፡
  10. ማስታወቂያው  ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ይሆናል፡፡
  11. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ሰነድ ማብራሪያ የሚያስፈልገው ከሆነ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  12. ተጫራቾች ጨረታውን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም፡፡
  13. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ድርጅቱ በውሉ መሰረት እቃዉን ባያቀርብ በውሉ በተመለከተው የገንዘብ መጠን ላይ በየቀኑ1 ወይም 1/100 መቀጫ እንዲከፍል ይደረግና በዚህ አይነት የሚታሰበው የውሉ ዋጋ አስር በመቶ መብለጥ የለበትም፡፡
  15. ውሉ እንዲፈፀም መዘግየት በስራው እንቅስቃሴ ላይ ተጽእኖ የሚያስከትል ከሆነ የመንግስት መስሪያ ቤቱ በመቀጫው መጠን አስር በመቶ እስኪሞላ ድረስ መጠበቅ ሳይገደድ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን መሰረዝ ይችላል ፡፡
  16. ኮሌጁ በጨረታ ካሸነፈው ተጫራቾች ላይ 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አላቸው፡፡
  17.  ኮሌጁ አሸናፊውን የሚለየው በነጠላ ዋጋ ነው፡፡

ማሳሰቢያ ፡- ውል ከወሰዱበት የጊዜ ገደብ ውስጥ እቃውን ባያስገቡ በውሉ መሰረት የሚቀጡ መሆኑን እየገለፅን ለ2ኛ አሸናፊ ይሰጣል  ወይም ኮሌጅ ለስራ በሚያመቸው መንገድ የምንሰራ  መሆኑን  ተገንዝበው  በተባለው ጊዜ ብቻ እንዲያቀርቡ እንገልፃለን፡፡

የነፋስ መውጫ /ፖ/ቴ/ ኮሌጅ

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here