ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
89

የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የሚፈልጋቸውን ሎት 1  ፕላስቲክ የውኃ ማስተላለፊያ ቱቦ (HDPE Pipes) ፣ሎት 2 የብየዳ ጀኔሬተር (ዌልዲንግ ጀኔራር) ፣ሎት 3 የደንብ ልብስ እና ሎት 4 የውኃ ማጣሪያ ኬሚካል (ኮፐር ሳልፌት) በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መረጃዎች በማቅረብ በጨረታዉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ /ቫት/ የሆኑ፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት የጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ህጋዊ /ሲፒኦ/ ብቻ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ጎ/ከ/ው/ፍ/አገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 27 በመግዛት በጨረታ ዝርዝሩ መሰረት ዋጋቸውን በመሙላትና በፖስታ በማሸግ ከቀን 21/05/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 05/06/2017 ዓ.ም ጠዋቱ 4፡00 ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 14 ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የተወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ተለያይቶ በታሸገ ኢንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል /ቴክኒካልና ፋይናንሻል እና አንድ ኮፒ/ ቴክኒካልና ፋይናንሻል/ የያዙ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው ከቀን 21/05/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀን 05/06/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
  9. ጨረታው በተመሳሳይ በቀን 05/06/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታው መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ በአገር አቀፍ በዓል ካልተዘጋ በስተቀር ዘወትር ቅዳሜ እስከ 6፡00 የሥራ ቀን ሲሆን ይህም እንደ አንድ የሥራ ቀን ይቆጠራል፡፡
  11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 211 33 16 /058 112 06 97 በመደወል ማነጋገር ይችላሉ፡፡

የጎንደር ከተማ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here