በደቡብ ወሎ መስተዳደር ዞን የአጅባር ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የአጅባር ከተማ የውስጥ ለውስጥ አዲስ እና ነባር የፕላን መንገድ ለመክፈት የሚያስፈልጉ የተለያዩ ለሥራው ተዛማጅ የሆኑ ማሽኖችን በሰዓት በመከራየት በዘርፉ ተሰማሩ ህጋዊ ባለሀብቶችን ድርጅቶችን በማወዳደር በግልጽ ጨረታ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚያስፈልጉት ማሽኖች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡ 1ኛ ግሪደር (CAL) በቁጥር 1 /አንድ/ ፣2ኛ ኤክስካቫተር ባለ ሰንሰለቱ ብዛት በቁጥር 1 (አንድ) 320 እና በላይ የፈረስ ጉልበት ያለው ፣3ኛ ገልባጭ መኪና (ሲኖ ትራክ) ብዛት በቁጥር 6 (ስድስት) ጎማቸው አዲስ የሆነ እና ጥራት ያለዉ 16 ሜ/ኩ እና በላይ የሚይዝ ከማቴሪያል ቦታ በአማካኝ 6 ኪ.ሜ በሆነ ርቀት ውስጥ የማጓጓዝ ሥራ የሚሰራ ፣4ኛ ሮሎ ብዛት በቁጥር 1 (አንድ) Why vibeveratr 18 ቶን እና በላይ የመምታት አቅም ያለው እና 5ኛ ሻወር ትራክ በቁጥር 1 (አንድ) 16000 ሊትር እና በላይ የሚይዝ የመኪና ጎማዉ አዲስ የሆነና ጥራት ያለዉ መሆን አለበት ፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ማሽኖች ሞዴላቸው ከ2014-2023 እ.እ.አ የሆነ ሲሆን በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በሥራ ዘርፉ የ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑ የሥራ ግብር ክፍያ የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ መጠን ከ200,000.00 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም /ቫት/ ከፋይ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- እያንዳንዱ ዋጋ የሚሞላው በነፃ ገበያ ላይ ተመስርቶ መሆን አለበት፡፡
- በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች የአንድ ማሽን ሙሉ የሥራ ወጭ ዋጋ እና የጠቅላላ ማሽን የሥራ ውጭ ዋጋ መሙላት ያለባቸው ሲሆን ተጫራቹ የሚለየው በሎት በጠቅላላ ዋጋ ነው፡፡
- ተጫራቾች የቴክኒክ ብልሽቶች የስፔር ፓርቶች ለውጦች እንዲሁም ለሁሉም ማሽነሪዎች ማሰሪያ ነዳጅ ዘይት የማሽን ቅባት ተጫራቾች በራሳቸዉ ወጭ ይሸፍናሉ፡፡ ዝናብ ሲጥል ሰዓቱ የማይቆጠር ይሆናል፡፡
- የማሽን ኪራይ ሰዓት የሚቆጠረው ለሠራው ሥራ ሰዓት ብቻ ነው የተፈጥሮ አደጋዎች ዝናብ ሲጥል ሰዓቱ የማይቆጠር ይሆናል፡፡
- የማሽን ማጓጓዝ እና መጫኛ ማውረጃ እንዲሁም ከሚሰራበት ሳይት ወደ ሌላ 6 ኪ/ሜ ርቀት ባለው የገረጋንቲ ማምረቻ ቦታ ማጓጓዝ መጫን ማውረድ ተጫራቹ የሚችል ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሹፌር እና የኦፕሬተር እንዲሁም የረዳት አበል እና ሌሎች ወጭዎች የሚችሉ እና የስነ ምግባር ችግር የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታ ሰነዱ የሚሽጥበት ቦታ ደ/ወ/ዞ አጅባር ከተማ መሪ ማ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ከ19/05/017 እስከ 09/06/2017 ዓ.ም 11፡00 ድረስ በመቅረብ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት የምትችሉ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር ከ1-10 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በፖስታ አሽገው ማስገባት አለባቸው እና ኦርጅናል ዶክመንቶችን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አሽገው የተጫራቾችን ስምና አድራሻ በመጻፍ በማህተም እና ፊርማ አስደግፈው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ግልጽ ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሥራውን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ ደረሰኝ ማረጋገጫ ሲፒኦ ለደ/ወ/ዞ አጅባር ከተማ መሪ ማ/ቤት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ደ/ወ/ዞ አጅባር ከተማ መሪ ማ/ቤት በጨረታ ኮሚቴው ቢሮ ቁጥር 7 በመገኘት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ22ኛው የሥራ ቀን በ10/06/2017 ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 4፡00 ድረስ ብቻ የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ፖስታ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በ21ኛው ቀን ማለትም በ09/06/2017 የሥራ ቀን ባለመሆኑ ምክንያት ጨረታው በደ/ወ/ዞ አጅባር ከተማ መሪ ማ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ22ኛው የሥራ ቀን 10/06/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 441 05 23 /09 21 97 05 64 /09 14 06 56 11 ደውለው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
አጅባር ከተማ መሪ ማ/ቤት