የመካነ ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንኡስ አንቀፅ 1 መሠረት በ2017 በጀት አመት 1ኛ ዙር በመደበኛ ጨረታ ለመኖሪያ 21 ፣ ለድርጅት 4 አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
- መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሠው ወይም ድርጅት ከ19/05/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 07 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ መሸጥ ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በቢሮ ቁጥር 07 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በቀኑ 11፡00 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በ3፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በከተማ አስተዳደር አዳራሽ ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በጽ/ቤቱ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ ወይም በስልክ ቁጥር 058 447 07 07 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ቦታውን ለመጐብኘት የሚፈልግ አካል በ20/05/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡00 ከተማ አገልግሎት ቢሮ በመምጣት ከኮሚቴው ጋር በመገናኘት መጐብኘት ይቻላል፡፡
የመካነ ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት