በአዊ ብሄረሰብ ዞን የአዲስ ቅዳም ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት ሎት 1 የጽ/መሳሪያ እና ቋሚ አላቂ ዕቃ ፣ሎት 2 የጽዳት እቃዎች ፣ሎት 3 የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ሎካል ፈርኒቸር ፣ሎት 4 የቤትና የቢሮ ዕቃዋች ኢምፖርትድ ፈርኒቸር ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እንዲሁም ሎት 6 የቅየሳ መሳሪያ (ቶታል ስቴሽን) እና ጀነሬተር በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ እያንዳንዱን ሎት በተናጠል አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳዳር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- የዘመኑ የታደሠ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የግዥው /የአገልግሎቱ/ መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሠነድ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን እያንዳንዱን ሎት በማይመለስ 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል አዲስ ቅዳም ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ / ወይም የዕቃውን /አገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ አዲስ ቅዳም ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት ህጋዊ ደረሰኝ መሂ 1 ተቆርጦ ኮፒውን ከሠነዱ ጋር ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ በሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- እንደ በጀቱ አቅም ሃያ በመቶ የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በእያንዳንዱ ምድብ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት መስፈርቱን በማሟላት ከእያንዳንዱ በተናጠል ዋጋ ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ነው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ በ16ኛው ቀን 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሠዓት ተዘግቶ በዚሁ ሠዓት ይከፈታል፡
- አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 ሥራ ቀናት በኃላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ በአዲስ ቅዳም ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት በማስያዝ ውሉን መፈጸም ይኖርበታል፡፡ በተባለው ቀን መጥቶ ውሉን የማይፈጽም ከሆነ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ውል ከፈጸመ በኃላ የአሸነፋቸውን ዕቃዎች አዲስ ቅዳም ከተማ ድረስ አጓጉዞ ያደርሳል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ሰለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 450 06 59 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአዲስ ቅዳም ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት