የበጌምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ2017 በጀት አመት በመደበኛ በጀትና በውስጥ ገቢ በጀት ሎት1.የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያ፣ 2.የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ፣3.የጽዳት፣4.የተለያዩ የኤሌክትሪክ፣ 5.የተሸከርካሪ መለዋዎጫ ፣ 6.የቧንቧ ውሃ እቃዎችን 7.የተለያዩ ህትመቶች 8.የስፖርት ማሰልጠኛ እቃዎችን፣ 9.የሙዚቃ መሳሪያ እቃዎችን፣ 10.የኮስሞቲክስ እቃዎች ፣11.የህንጻ መሳሪያ እቃዎች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል 12. የተሸከርካሪዎች ጥገና ለ2 ዓመት ውል ተይዞ ጥገና ለማድረግ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸዉ፡፡
- የንግድ መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠኑ ከ200,000.00 (ሁለት መቶ ሽህ)ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ኮሌጁ ከብር 20,000.00 /ሃያ ሽህ/ ብር በላይ ግዥ ሲፈጽም መንግስት በሰጠው ውክልና መሰረት 7.5 በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቀንሶ ያስቀራል፡፡
- ኮሌጁ ከብር 10,000.00 /አስር ሽህ/ ብር በላይ ግዥ ሲፈጽም ሁለት በመቶ የዊዝሆልዲንግ ታክስ ቀንሶ ያስቀራል ፡፡
- በሰነዱ ላይ የተጠቀሰዉ ቁጥር ብዛት ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- ተጫራች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የሚገዙትን እቃዎች ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ/ ብር በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሞሉትን የእቃዉን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ የገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ኮፒዉን ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች አሸናፊነታቸው ተገልጾላቸው ያሸነፉትን የዕቃ ጠቃላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪ ዋስትና /ሲ.ፒ.ኦ./ ወይም በጥሬ ገንዘብ የገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ዋናዉን ብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 16 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 9 በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡10 ይከፈታል፡፡
- ዉድድሩን በተናጠል የምናወዳድር ሲሆን ተጫራቾች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሰዉ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- አሸናፊዎች እቃዎቹን ከኮሌጁ ድረስ በማጓጓዝ ንብረት ክፍል ገቢ በማድረግ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0581410031 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አድራሻ ደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ደ/ታቦር ከተማ (በጌምድር መ/ራን ትም/ኮሌጅ
የበጌምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ