የእብናት ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለፍ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽፈት እቃዎች ፣ሎት 2 ፈርኒቸር ፣ ሎት 3 ህትመት ፣ ሎት 4 የሌሌክትሮኒክስ ፣ሎት 5 የጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- የገዥው መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መስረያ ቤቱ በሎት በተናጠል ዋጋ በሞሉት የሚያወዳድር ይሆናል፡፡
- ማንናቸውም ተጫራች ከሚወዳደረበት ሎት ውስጥ ሁሉንም ካልሞላ ከጨረታ ውጭ ይደርጋል፡፡
- ፍ/ቤቱ በአጠቃላይ እንዲገዛ ካዘዘው እቃዎች ላይ ሃያ በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
- የሚገዛውን እቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡ ሆኖም ስፔስፊኬሸን ሳይሞላ ክፍት ያደረገ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ00 /ሃምሳ ብር/ በመከፈል ግ/ፋ/ን/አስ/ቡ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚወዳደረበት ብር የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና /በጥሬ ገንዘብ/ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግ/ፋ/ን/አስ/ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 12 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከ26/05/2017 እስከ 26/06/2017 ለ1 ወር ተከታታይ ቀን ከቆየ በኋላ በ27/06/2017 ዓ.ም ቀኑ የህዝብ በዓል ከሆነ ተከታታይ ባለው ቀን ከ3:00 በኋላ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ን/አስ/ጉ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 12 ከ3፡00 በኋላ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፏቸውን እቃዎች ከመ/ቤቱ እ/ወ/ፍ/ቤት ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው እንደ አስፈላጊነቱ ለ6 ወር ኮንትራት ውል አገልግሎት ሊወስድ ይችላል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ መሆን የሚችለው በየሎቱ በተናጠል ዋጋ ዝቅተኛ የዋጋ መጠን የሞላ ነው፡፡
- የሚያቀርቡት እቃ በተጠየቀው ስፔስፊኬሽን እና በናሙናው መሰረት መሆን አለበት፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 12 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 440 01 23 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
የእብናት ወረዳ ፍ/ቤት