ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
88

በደቡብ ጎን/ዞን የሃሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሀሙሲት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በከተማው ውስጥ ለሚያሰራው የኮበልስቶን ንጣፍና የካልበርት ጥገና ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
  2. የግብ ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉና ማስረጃ ያላቸው፡
  3. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሽህ/ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡
  5. የስራ ዝርዝሩ መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር00/ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል ከረዳት ገንዘብ ያዥ ክፍል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ለዉድድር ያስቀመጡትን ዋጋ 2 በመቶ ከመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብቻ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ያስያዙትንም ሲፒኦ ወይም የገቢ ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማስገባት አለባቸዉ፡
  8. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡንና ማስረጃዎችን ዋናዉን በጥንቃቄ በታሸገ በአንድ ፖስታ ለሐሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን ተብሎ ተጽፎበት ቢሮ ቁጥር 4 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ጨረታዉ በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 16ኛዉ ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይቻላል ፡፡ የሚታሸገዉም በዚሁ ሰዓት ይሆናል ፡፡
  9. የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በገንዘብ ጽ/ቤት በ16ኛዉ ቀን 4፡00 በጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴው ይከፈታል ፡፡
  10. አሸናፊዉ ማሸነፉ ከተገለጸለት ከ5 ቀናት በኋላ ባሉት 5 የስራ ቀናት ዉስጥ ገንዘብ ጽ/ ቤት ቀርቦ ባሸነፈበት ገንዘብ መጠን ልክ የዉል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ዉል መዉሰድ ያለበት ሲሆን በወቅቱ ቀርቦ ዉል ካልወሰደ በግዥ መመሪያዉ መሰረት አስፈላጊዉን እርምጃ ይወሰዳል፡፡
  11. የስራው ርክክብ የሚፈጸመዉ በባለሙያ ከተረጋገጠ በኋላ በሃሙሲት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
  12. የጨረታ መክፈቻዉ ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከናወናል ፡፡
  13. የጨረታ አሸናፊዉ የሚለየዉ ለሁሉም ስራዎች በሰጠዉ ጥቅል ዋጋ ድምር የሚወስን ሲሆን በሰነዱ ዋጋ መሙያ ቦታ ላይ አንዱንም የስራ ዝርዝር ያልሞላና ስርዝ ድልዝ ያደረገ ተጫራች ከጨረታ ዉጭ ይሆናል ፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ ፡፡
  15. ስለ ጨረታዉ ዘርዝር መረጃና ማብራሪያ ከፈለጉ ሃሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0584430320 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ ፡፡

የሃሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here