ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
82

በአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለ2017 በጀት አመት ለተቋሙ አገልግሎት የሚዉሉ ልዩ ልዩ አቅርቦቶችን ማለትም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣የህትመት ሥራዎች እና የህክምና ግብዓት አቅርቦቶችን በመደበኛ እና ከረጅ ድርጅቶች በተገኘ የበጀት ድጋፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መሰፈረቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ወይም ተከታታይ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥው መጠን 200,00000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የጨረታውን አይነትና ዝርዝር መግለጫ / ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 00 /አንድ መቶ ሃምሣ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአማረኛ ቋንቋ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ መሰረት የአንዱን ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ድምር ዋጋ ከነ ቫቱ በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፣ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማሸግ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ኢንስቲትዩቱ ባዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱ የሚሸጠዉ ጨረታዉ በአየር ላይ ከዋለ እስከ 15ኛዉ ቀን ከቀኑ 11፡30 ብቻ ይሆናል፡፡
  9. ጨረታዉ በ16 ኛዉ ቀን የጨረታ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡05 ላይ ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 25,00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ፣በባንክ ጋራንቲ ወይም በተቋሙ የባንክ አካዉንት ገቢ በማድረግ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  11. ኢንስቲትዩቱ የጨረታ አሸናፊዉ ከተለዬ በኋላ እንደ ተቋሙ በጀት ሃያ በመቶ በመጨመር ወይም በመቀነስ ውል ይዞ የማስቀረብ መብት ይኖረዋል፡፡
  12. የጨረታው አሸናፊው የሚለየው ከህክምና ግብዓት ዉጭ በሎት ምድብ በድምር   ዋጋ ይሆናል፡፡
  13. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 32 38 በሥራ ሠዓት በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
  15. ኢንስቲትዩቱ የሚሰበስበው ሁለት በመቶ ዊዝ ሆልድ ብቻ ነዉ፡፡

አድራሻ፡- ፈለገ ህይወት ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ጎን

የአብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here