ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
89

በአብከመ የሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. የጽህፈት መሳሪያ ፣ሎት2. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት3. የውሃ እቃዎች፣ ሎት4.የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት5. የኤሌክትሪክ እና የህንጻ እቃዎች፣ ሎት6. ህትመት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡

  1. ተጫራቾች እቃዎችን ወይም አገልግሎቾችን ለማቅረብ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣የተሰጣቸው ፈቃድ አንድ አመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ  የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ/ ከገንዘብ ያዥ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማርኛ መሆን ይኖርበታል፡፡
  8. በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ በማያሻማ ሁኔታ በመሙላት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል ፡፡
  10. አንድ ተጫራች በወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ቢያስፈልግ ጨረታውን ላወጣው መስሪያ ቤት በፅሁፍ ወይም በፋክስ ቁጥር 058661ዐ264 ወይም በስልክ ቁጥር 058661ዐ330 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል ፡ጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤትም የተጠየቀውን ጥያቄ ማብራሪያ የሚያሰጥ ሆኖ ሲገኝ ለሁሉም ተጫራቾች በጽሁፍ ወይም በፋክስ ጨረታው ከመከፈቱ ከ5 ቀናት በፊት መልስ ይሰጣል፡፡
  11. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
  13. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን እሁድ ቅዳሜና በዝግ ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተጠየቀው ስዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  14. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች አሸናፊው ከተለየ በኋላ የሚመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 4,000 /አራት ሽህ/ ብር ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

የሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here